ስለዚህ እጁን አንሥቶ በመማል በበረሓ የሚያጠፋቸው መሆኑን ነገራቸው፤
በምድረ በዳ ሊጥላቸው፣ እጁን አንሥቶ ማለ፤
በምድረ በዳም ይጥላቸው ዘንድ፥ ዘራቸውንም በአሕዛብ መካከል ይጥል ዘንድ፥ በየአገሩም ይበትናቸው ዘንድ፥ እጁን አነሣባቸው።
ወደ ሰማይ ይወጣሉ፥ ወደ ጥልቅም ይወርዳሉ፤ ሰውነታቸውም በመከራ ቀለጠች።
ተቈጥቼም ‘ዕረፍት ወደምታገኙባት ምድር ከቶ አትገቡም’ ብዬ ማልኩ።”
ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ አወርሳቸው ዘንድ በመሐላ ቃል ኪዳን ወደገባሁባት ምድር አመጣችኋለሁ፤ ርስትም አድርጌ አወርሳችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ”
ከዚህም በላይ ከዓለም ምድር ሁሉ ውብ የሆነችውንና በማርና በወተት የበለጸገችውን ምድር እሰጣችኋለሁ ብዬ ቃል ገብቼላቸው ነበር። ከዚያ በኋላ ግን በበረሓ እያሉ ወደዚያ እንደማላስገባቸው አረጋግጬ ነገርኳቸው።
ደግሞም፥ “ ‘እኔ ወደምሰጣቸው የዕረፍት ቦታ ከቶ አይገቡም!’ ብዬ በቊጣዬ ምዬአለሁ።”
ደግሞስ እነዚያን ያልታዘዙትን ካልሆነ በቀር “ወደ ዕረፍቴ አትገቡም” ብሎ የማለባቸው እነማን ነበሩ?