መዝሙር 106:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ሕዝቦቹን ለማጥፋት ዐቅዶ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የመረጠው ሙሴ በመካከል በመቆም፥ እንዳያጠፋቸውና ቊጣውንም እንዲመልስ እግዚአብሔርን ለመነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በመቅሠፍቱ እንዳያጠፋቸው ይመለስ ዘንድ፣ እርሱ የመረጠው ሙሴ በመካከል ገብቶ፣ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፣ እንደሚያጠፋቸው ተናግሮ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዳያጠፋቸው ቁጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ያጠፋቸው እንደ ነበረ ተናገረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመርከቦች ወደ ባሕር የሚወርዱ፥ በብዙ ውኃ ሥራቸውን የሚሠሩ፥ |
የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! “እስቲ በኢየሩሳሌም መንገዶች ሁሉ እየተዘዋወራችሁ እዩ! ትክክለኛ ፍርድ የሚሰጥና እውነትን የሚሻ አንድ ሰው እንኳ ማግኘት ትችሉ እንደ ሆነ፥ እስቲ በየአደባባዩ ፈልጉ! ይህ ቢሆን እኔ ለኢየሩሳሌም ምሕረት አደርግላታለሁ።
ነገር ግን እነርሱ ዐመፀኞች ሆኑ እንጂ እኔን ለማዳመጥ ፈቃደኞች አልሆኑም፤ ዐይኖቻቸው ያተኰሩባቸውን አጸያፊ ምስሎች አላስወገዱም፤ የግብጽንም ጣዖት ማምለክ አልተዉም፤ ስለዚህ በግብጽ በነበሩበት ጊዜ ቊጣዬን ላወርድባቸው አስቤ ነበር።
በቊጣዬ አገሪቱን ከማጥፋቴ በፊት የቅጽር ግንብ የሚሠራ፥ ቅጽሮቹ በፈረሱበት በኩል በመቆም በእኔና በሕዝቡ መካከል ገብቶ ቊጣዬን የሚያበርድ ሰው ፈለግኹ፤ ነገር ግን ማንንም አላገኘሁም።
ቆሬንና ተከታዮቹን እንዲህ አላቸው፦ “ነገ ጠዋት እግዚአብሔር ለእርሱ የተለየ ማን እንደ ሆነ ለይቶ ያሳየናል፤ ይኸውም የእርሱ የሆነውንና የመረጠውን በመሠዊያው ላይ ያገለግለው ዘንድ ወደ እርሱ እንዲቀርብ ይፈቅድለታል።
“እነሆ! የመረጥኩት አገልጋዬ ይህ ነው! እርሱ እኔ የምወደውና የምደሰትበት ነው፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ እርሱም ቅን ፍርድን ለሕዝቦች ያውጃል።
እኔ መረጥኳችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም ነዋሪ እንዲሆን ሾምኳችሁ። ስለዚህ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ይሰጣችኋል።
የዓለም ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን በወደደ ነበር፤ ነገር ግን የዓለም ስላልሆናችሁና እኔ ከዓለም ለይቼ ስለ መረጥኳችሁ፥ ዓለም ይጠላችኋል።
“እኔም ከዚህ በፊት ባደረግሁት ዐይነት እንደገና በተራራው ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በመጸለይ ቈየሁ፤ እግዚአብሔርም እንደገና ልመናዬን ሰምቶ አንተን ላለማጥፋት ፈቀደ።
“ከዚያም ሁሉ የተነሣ በእግዚአብሔር ፊት በግንባሬ ተደፍቼ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቈየሁ፤ ይህንንም ያደረግኹት እርሱ ‘እደመስሳችኋለሁ’ ብሎ ስለ ነበር ነው፤
ስለዚህ እንድትፈወሱ ኃጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ እያንዳንዱም ለሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት ብዙ ውጤት የሚያስገኝ ታላቅ ኀይል አለው፤