አንተ ወዳዘጋጀህለት ስፍራ፥ ወደ ተራራዎች ላይና ወደ ሸለቆዎች ውስጥ ፈሰሰ።
በተራሮች ላይ ፈሰሱ፤ ወዳዘጋጀህላቸው ስፍራ፣ ወደ ሸለቆዎች ወረዱ።
ወደ ተራሮች ይወጣሉ፥ ወደ ቈላዎች፥ ወዳዘጋጀህላቸው ስፍራ ይወርዳሉ፥
ለዘለዓለም የሚኖር ቃል ኪዳኑን፥ እስከ ሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን ዐሰበ።
ውሃው እስከ ዐሥረኛው ወር ድረስ ቀስ በቀስ እየጐደለ ሄደ፤ በዐሥረኛው ወር መጀመሪያው ቀን የተራሮቹ ጫፎች ታዩ።
ባሕርን ሁሉ በአንድ ቦታ ሰበሰበ፤ ጥልቅ ለሆኑት ውቅያኖሶችም መከማቻ ስፍራ አዘጋጀላቸው።
ተራራዎችና ኰረብቶች ከመመሥረታቸው በፊት ተወለድኩ።