በላዩ መርከቦች ይመላለሳሉ፤ በውስጡም አንተ የፈጠርከው ሌዋታን የተባለ ታላቅ ዘንዶ ይጫወታል።
መርከቦች በላይዋ ይመላለሳሉ፤ አንተ የፈጠርኸውም ሌዋታን በውስጧ ይፈነጫል።
በዚያ ላይ መርከቦች ይሄዳሉ፥ በዚያም ላይ የፈጠርኸው ዘንዶ ያጫውትሃል።
ባሪያውን ሙሴን፥ የመረጠውንም አሮንን ላከ።
“ዛብሎን በባሕር ዳር ይኖራል፤ ወደቡም የመርከቦች ማረፊያ ይሆናል፤ የመኖሪያውም ወሰን እስከ ሲዶና ይደርሳል።
ውሃ በምድር ላይ እያደገና እየበረታ በሄደ መጠን መርከቡ በውሃው ላይ መንሳፈፍ ጀመረ።
ሌዋታንን መቀስቀስ የሚችሉና ቀኖችን የሚረግሙ አስማተኞች ያን ቀን ይርገሙት።
አንዳንዶች በመርከብ ተሳፍረው በታላቅ በባሕር ላይ እየተጓዙ ንግዳቸውን ያካሂዱ ነበር።
ሌዋታን የተባለውን የባሕር ዘንዶ ራስ ቀጠቀጥህ፤ ሥጋውንም በበረሓ ለሚኖሩ ፍጥረቶች ምግብ አድርገህ ሰጠሃቸው።
በዚያን ቀን እግዚአብሔር በጽኑ፥ በታላቁና በኀያል ሰይፉ የሚስለከለከውንና የሚጠመጠመውን እባብ ሌዋታንን ይቀጣል፤ የባሕሩንም ዘንዶ ይገድላል።
የተበላሸውን ለመጠገን በጌባል ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎች በአንቺ መካከል ነበሩ፤ መርከበኞች በመርከባቸው ወደ ወደብሽ እየመጡ ከአንቺ ጋር ይገበያዩ ነበር።’