ፀሐይ በሚወጣበት ጊዜ ሾልከው ይሄዳሉ፤ ተመልሰው በየመኖሪያቸው ውስጥ ይተኛሉ።
ፀሓይ በወጣች ጊዜም ይመለሳሉ፤ በየጐሬያቸውም ገብተው ይተኛሉ።
ፀሐይ ስትወጣ ይሰበሰባሉ፥ በየዋሻቸውም ይተኛሉ።
አለቆቹን ሁሉ እንደ እርሱ ይገሥጽ ዘንድ፥ ሽማግሌዎቹንም እንደ እርሱ ጥበበኞች ያደርጋቸው ዘንድ።
በዚያን ጊዜ የዱር አውሬዎች ሸሽተው ወደየመሸሸጊያቸው ይገባሉ፤ በየዋሻቸውም ውስጥ ይሰወራሉ።
ጠባቂዎችሽ እንደ ኲብኲባ፥ ባለ ሥልጣኖችሽ በብርድ ቀን በአጥር ላይ እንደ ሰፈረ የአንበጣ መንጋ ናቸው፤ ፀሐይ ሲወጣ በረው ይሄዳሉ፤ ወዴት እንደሚሄዱ ግን የሚያውቅ የለም።
ክፉ ነገር የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላል፤ ክፉ ሥራውም እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም።