መዝሙር 104:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰማይ ዝናብን በተራሮች ላይ ታወርዳለህ፤ ምድርም በምትሰጣት በረከት ትሞላለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከላይ ከእልፍኝህ ተራሮችህን ታጠጣለህ፤ ምድርም በሥራህ ፍሬ ትረካለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተራሮችን ከላይ የምታጠጣቸው፥ ከሥራህ ፍሬ ምድር ትጠግባለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሕዝብ ወደ ሕዝብ፥ ከነገሥታት ወደ ሌላ ሕዝብ አለፉ። |
በእርሱ ትእዛዝ ከሰማይ በላይ ያሉ ውሃዎች የመናወጥ ድምፅ ያሰማሉ፤ እርሱ ደመናዎችን ከምድር ዳርቻ ያመጣል፤ በዝናብ ጊዜም መብረቅ እንዲበርቅ ያደርጋል፤ ነፋስንም ከማከማቻው ይልካል።
ከአሕዛብ አማልክት መካከል አንዱ እንኳ ዝናብ ማዝነብ አይችልም፤ ሰማይም በራሱ ፈቃድ ካፊያ አያወርድም፤ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! ይህን ሁሉ የምታደርግ አንተ ስለ ሆንክ እኛ ተስፋ የምናደርገው በአንተ ነው።
ይህን ብታደርጉ፥ በሰማይ ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆናላችሁ። እርሱ ለክፉዎችና ለደጎች ፀሐዩን ያወጣል፤ እንዲሁም ለጻድቃንና ለግፈኞች ዝናቡን ያዘንባል።
ይሁን እንጂ እርሱ እንዴት ያለ ቸር አምላክ መሆኑን የሚመሰክር መልካም ሥራ ማድረጉን አላቋረጠም፤ ከሰማይ ዝናብን አዘነበላችሁ፤ የመከር ወራትንም ሰጣችሁ፤ በምግብና በደስታ ልባችሁን አረካ።”