ሰማይ ከምድር ከፍ የሚለውን ያኽል እግዚአብሔር ለሚፈሩት የሚሰጠው ፍቅር ታላቅ ነው።
ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣ እንዲሁ ለሚፈሩት ምሕረቱ ታላቅ ናት።
ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ ምሕረቱን በሚፈሩት ላይ አጠነከረ።
የዱር አራዊትን ሁሉ ያጠጣሉ፥ የበረሃ አህዮችም ጥማታቸውን ያረካሉ።
“እግዚአብሔር ከፍ ባለው ሰማይ የሚኖር አይደለምን? ከዋክብት ምንም እንኳ ከፍ ባለ ስፍራ ቢሆኑ፥ እርሱ ከበላያቸው ሆኖ ይመለከታቸዋል።
ነገር ግን እግዚአብሔር ለሚያከብሩት ሁሉ ፍቅሩን ለዘለዓለም ያሳያቸዋል፤ ቸርነቱም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል።
እርሱ ለእኛ ያለው ፍቅር ጽኑ ነው፤ ታማኝነቱም ዘለዓለማዊ ነው። እግዚአብሔር ይመስገን!
ከሚያሤሩባቸው ሰዎች በመኖሪያህ ጥላ ሥር ትደብቃቸዋለህ፤ ከመርዘኛ አንደበትም በከለላህ ትጠብቃቸዋለህ።
እግዚአብሔር ሆይ፥ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ እስከ ሰማይ፥ እውነተኛነትህም እስከ ደመና ይደርሳል።
ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ከሰማያት በላይ ነው፤ ታማኝነትህም ወደ ጠፈር ይደርሳል።
ፍቅርህ ለዘለዓለም እንደሚጸናና ታማኝነትህን እንደ ሰማይ እንደሚመሠረት እናገራለሁ።
ንጉሥ የሚያስበውን ማወቅ አትችልም፤ የንጉሥ አሳብ እንደ ሰማይ የመጠቀ እንደ ውቅያኖስ የጠለቀ ነው።
ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ መንገዴ ከመንገዳችሁ፥ ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እጅግ ከፍ ያለ ነው።
እግዚአብሔር ለሚፈሩት ሰዎች ሁሉ ከትውልድ እስከ ትውልድ ምሕረቱን ያደርጋል።