እንቅልፍ ከቶ በዐይኔ አይዞርም፤ በቤት ጣራ ላይ እንዳለ ብቸኛ ወፍ ሆኜአለሁ።
ያለ እንቅልፍ አድራለሁ፤ በቤቴ ጕልላት ላይ እንዳለ ብቸኛ ወፍ ሆንሁ።
እንደ ምድረ በዳ እርኩም መሰልሁ፥ በፈረሰ ቤት እንዳለ እንደ ጉጉት ሆንሁ።
ለሙሴ መንገዱን አሳየ፥ ለእስራኤል ልጆችም ፈቃዱን።
ከሰው ተለይቼ ለቀበሮ ወንድም ለሰጎንም ባልንጀራ ሆንኩ።
ንጋትን ከሚጠባበቁ ጠባቂዎች ይልቅ እኔ እግዚአብሔርን በናፍቆት እጠባበቃለሁ።
አምላኬ ሆይ! በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አትሰማኝም፤ በሌሊት እጣራለሁ፤ ዕረፍትም የለኝም።
ወዳጆቼና ጓደኞቼ ሕመሜን ተጸየፉ፤ ዘመዶቼም ከእኔ ራቁ፤
ሌሊቱን ሙሉ አነቃኸኝ፤ ጭንቀቴም ስለ በዛ መናገር አልቻልኩም።