እነሆ፥ አሁንም የእኔን ጸሎት ስማ፤ አንተን ማክበር የሚወዱትን የሌሎችንም አገልጋዮችህን ጸሎት አድምጥ፤ ዛሬ ልሠራው ያቀድኩት ይሳካልኝ ዘንድ የንጉሠ ነገሥቱን ልብ በማራራት እርዳኝ።” እነሆ፥ እኔ በዚህ ጊዜ የንጉሠ ነገሥቱ ወይን ጠጅ አሳላፊ ነበርኩ።
መዝሙር 102:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የድኾችን ጸሎት ይሰማል፤ ልመናቸውንም አይንቅም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል፤ ልመናቸውንም አይንቅም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ጽዮንን ይሠራታልና፥ በክብሩም ይገለጣልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ይቅርታው ግን ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚፈሩት ላይ፥ ጽድቁም በልጅ ልጆች ላይ ነው፤ |
እነሆ፥ አሁንም የእኔን ጸሎት ስማ፤ አንተን ማክበር የሚወዱትን የሌሎችንም አገልጋዮችህን ጸሎት አድምጥ፤ ዛሬ ልሠራው ያቀድኩት ይሳካልኝ ዘንድ የንጉሠ ነገሥቱን ልብ በማራራት እርዳኝ።” እነሆ፥ እኔ በዚህ ጊዜ የንጉሠ ነገሥቱ ወይን ጠጅ አሳላፊ ነበርኩ።
እግዚአብሔር ሆይ! አገልጋዮችህ ስለ ሆኑት የእስራኤል ሕዝብ ደኅንነት ቀንና ሌሊት የማቀርበውን ጸሎቴን ስማ፤ እኔንም አስበኝ፤ እኛ እስራኤላውያን የሠራነውንም ኃጢአት እናዘዛለሁ፤ በእርግጥም እኔና የቀድሞ አባቶቼ በደል ሠርተናል።
እኔም “የሰማይ አምላክ ሥራችንን ለማከናወን ይረዳናል፤ እኛ የእርሱ አገልጋዮች ነን፤ ስለዚህም ሥራውን እንጀምራለን፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ምንም ዐይነት ንብረት የማግኘት መብት ሆነ የታሪክ መታሰቢያነት አይኖራችሁም” ብዬ መለስኩላቸው።
የአገልጋዮቼን መልእክት አጸናለሁ፤ የነቢያቴንም ትንቢት እንዲፈጸም አደርጋለሁ፤፥ እነርሱም ኢየሩሳሌም፦ ‘የብዙ ሕዝብ መኖሪያ ትሆናለች፤ የይሁዳ ከተሞችም እንደገና ይሠራሉ፤ ፍርስራሾቻቸውም ይታደሳሉ’ ይላሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከሐናንኤል መጠበቂያ ግንብ ጀምሮ እስከ ማእዘኑ የቅጽር በር ድረስ ኢየሩሳሌም የእኔ ከተማ ሆና የምትታነጽበት ጊዜ ይመጣል።