መዝሙር 102:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ጽዮንን እንደገና በሚሠራበት ጊዜ በክብሩ ይገለጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ጽዮንን መልሶ ይሠራታልና፤ በክብሩም ይገለጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ አሕዛብ ስምህን፥ ነገሥታትም ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሱ ከእርሱ ይወጣልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ አይኖርምና ስፍራውንም ደግሞ አያውቀውምና። |
የቄዳር የበግ መንጋዎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ፤ የነባዮት አውራ በጎችም ለመሥዋዕትነት ያገለግሉሻል፤ በመሠዊያም ላይ ለመሥዋዕትነት ለመቅረብ ተቀባይነት ይኖራቸዋል። የተከበረውን ቤተ መቅደሴንም አስጌጣለሁ።
በጽዮን ለሚያለቅሱት ሰዎች በዐመድ ፈንታ የአበባ ጒንጒንን፥ በእንባቸው ምትክ የወይራ ዘይትን በኀዘን ፈንታ የደስታ ዘይትን፥ በዛለ መንፈሳቸው ፈንታ የምስጋና መጐናጸፊያን ለማስገኘት ላከኝ። እነርሱም ክብሩን እንዲገልጡ እግዚአብሔር የተከላቸው “የጽድቅ ዋርካዎች” ተብለው ይጠራሉ።
በሕዝቤ መካከል ያሉትን ሴቶች ከመልካም ቤት ንብረታቸው አፈናቅላችሁ አሳደዳችሁ፤ ልጆቻቸውንም ከእኔ በረከትና ክብር ዘወትር እንዲለዩ አደረጋችሁ።
እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በሕዝቦች ዘንድ የተከበረስለሆነ፥ ከበግ መንጋዎቹ መካከል አውራ በግ እያለው ለተሳለው ስለት ነውር ያለበትን በግ መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ የተረገመ ነው!” ይላል የሠራዊት አምላክ።