መዝሙር 101:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእግዚአብሔር ታማኞች የሆኑትን እመርጣለሁ፤ አገልጋዮቼም በሕይወታቸው ነቀፋ የሌለባቸው ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእኔ ጋራ ይኖሩ ዘንድ፣ ዐይኖቼ በምድሪቱ ታማኞች ላይ ናቸው፤ በፍጹም መንገድ የሚሄድ፣ እርሱ ያገለግለኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእኔ ጋር ይኖሩ ዘንድ ዐይኖቼ በምድር ምእመናን ላይ ናቸው፥ በቀና መንገድ የሚሄድ እርሱ ያገለግለኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ሜዳ አህያ ሆንኹ፤ ሌሊት በወና ቤት እንዳለ እንደ ጕጕት ሆንሁ። |
“አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድከኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እነዚህ አንተ የሰጠኸኝም እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር እንዲኖሩ እወዳለሁ።
እንዲህም የሚል ከፍተኛ ድምፅ ከዙፋኑ ሲወጣ ሰማሁ፤ “እነሆ! የእግዚአብሔር ማደሪያ ከሰዎች ጋር ነው፤ ከእነርሱም ጋር ይኖራል፤ እነርሱም የእርሱ ሕዝብ ይሆናሉ። እግዚአብሔር ራሱ ከእነርሱ ጋር ይሆናል፤ አምላካቸውም ይሆናል፤