የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ለነፍስ አዲስ ሕይወትን ይሰጣል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ የታመነ ነው፤ ማስተዋል ለጐደላቸው ጥበብን ይሰጣል።
ምሳሌ 8:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ዕውቀት የሌላችሁ፥ ዕውቀትን ለመገብየት ተማሩ፤ እናንተ ሞኞች፥ ማስተዋልን ገንዘብ አድርጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ አላዋቂዎች፤ ጠንቃቃነትን ገንዘብ አድርጉ፤ እናንተ ሞኞች፤ ማስተዋልን አትርፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ አላዋቂዎች፥ ማመዛዘንን ተረዱ፥ እናንተም ሞኞች አስተውሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ የዋሆች፥ ጥበብን አስተውሉ፤ እናንተም ሰነፎች፥ ዕውቀትን ገንዘብ አድርጉ፤ |
የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ለነፍስ አዲስ ሕይወትን ይሰጣል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ የታመነ ነው፤ ማስተዋል ለጐደላቸው ጥበብን ይሰጣል።
“እናንተ ዕውቀት የጐደላችሁ! እስከ መቼ ድረስ የሞኝነትን መንገድ ትከተላላችሁ! እናንተስ ፌዘኞች! እስከ መቼ ድረስ በማፌዝ ትደሰታላችሁ! ሞኞችስ እስከ መቼ ድረስ ዕውቀትን ትጠላላችሁ!
ዐይናቸውን እንድትከፍትላቸውና ከጨለማ ወደ ብርሃን እንድታወጣቸው ከሰይጣንም ግዛት ወደ እግዚአብሔር እንድትመልሳቸው አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በእኔ በማመናቸው ምክንያት የኃጢአታቸውን ይቅርታ ያገኛሉ፤ በተመረጡት መካከልም ርስትን ይካፈላሉ።’
እግዚአብሔር በዓለም ሰዎች ዘንድ አሉ ተብለው የሚታዩትን ነገሮች እንደሌሉ ለማድረግ በዓለም የተዋረደና የተናቀ ከንቱም መስሎ የሚታየውን ነገር መረጠ።