“ልጆቼ ሆይ! አድምጡኝ መንገዴን የሚከተሉ ይደሰታሉ።
“እንግዲህ፣ ልጆቼ ሆይ፤ አድምጡኝ፤ መንገዴን የሚጠብቁ ብፁዓን ናቸው።
አሁንም ልጆቼ ሆይ፥ ስሙኝ፥ መንገዴንም የሚጠብቁ ምስጉኖች ናቸው።
አሁንም ልጄ ሆይ፥ ስማኝ፥ መንገዴን የሚጠብቁ ብፁዓን ናቸው።
እኔ የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትያለሁ፤ ፊቴን ከአምላኬ በመመለስ ክፉ ነገር አላደረግሁም።
ጥፋትና ሞት ‘ስለ እርስዋ የምናውቀው፥ በወሬ ብቻ ነው’ ይላሉ።
እግዚአብሔርን የሚፈሩና ትእዛዞቹን በመጠበቅ የሚኖሩ ደስ ይበላቸው።
እኔ የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትዬአለሁ፤ ፊቴን ከአምላኬ በመመለስ ክፉ ነገር አላደረግሁም።
ከእግዚአብሔር የሚገለጥ መመሪያ ባይኖር ሕዝብ መረን ይለቀቃል፤ የእግዚአብሔርን ሕግ የሚያከብር ሰው ግን የተባረከ ነው።
ጥበብን የሚያገኝ፥ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ ሰው የተባረከ ነው።
ጥበብ፥ ለሚይዟት ሰዎች ሕይወትን ትሰጣለች፤ እርስዋንም ገንዘብ የሚያደርጉ የተባረኩ ናቸው።
ልጄ ሆይ! አድምጠኝ፤ እኔም ከምነግርህ ትምህርት አትራቅ።
እንግዲህ ልጄ ሆይ! አድምጠኝ፤ የምልህንም በጥንቃቄ ስማ፤
ኢየሱስ ግን “የተባረኩስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው በሥራ ላይ የሚያውሉት ናቸው፤” አላት።