ምሳሌ 8:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምክርና መልካም ጥበብ ከእኔ ይገኛሉ፤ ማስተዋልና ብርታትም የእኔ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክርና ትክክለኛ ጥበብ የእኔ ናቸው፤ ማስተዋል አለኝ፤ ብርታት አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክርና መልካም ጥበብ የእኔ ነው፥ ማስተዋል እኔ ነኝ፥ ብርታትም አለኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምክርና ሥልጣን የእኔ ናቸው፤ ማስተዋል የእኔ ነው፥ ብርታትም የእኔ ነው። |
ያብራራለት ዘንድ እግዚአብሔር ማንን አማከረ? ትክክለኛውን ፍርድ ያስተማረው ማነው? ዕውቀትን ያስተማረው፥ ወይም ትክክለኛውን መንገድ እንዲያስተውል ያደረገው ማነው?
እነሆ ሕፃን ተወልዶልናል! ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል! እርሱም መሪ ይሆናል፤ ስሙም “ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ” ይባላል።
ዓላማህ ታላቅ ነው፤ ሥራህም ኀያል ነው፤ ሕዝቦች የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ ታያለህ፤ ለእያንዳንዱም ሰው እንደአካሄዱና እንደየሥራው ዋጋውን ትከፍላለህ።
እናንተን ግን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አደረገ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ጥበባችን፥ ጽድቃችን፥ ቅድስናችንና ቤዛችን እንዲሆን አደረገው።