ጥበብን እንደ እኅትህ፥ ማስተዋልንም እንደ ቅርብ ወዳጅህ አድርገህ ቊጠራቸው።
ጥበብን፣ “እኅቴ ነሽ” በላት፤ ማስተዋልንም፣ “ዘመዴ ነህ” በለው፤
ጥበብን፦ “አንቺ እኅቴ ነሽ” በላት፥ ማስተማውልንም፦ “ዘመዴ” ብለህ ጥራት፥
ጥበብን፦ “አንቺ እኅቴ ነሽ” በላት፥ ማስተዋልንም፦ “ወዳጄ” ብለህ ጥራት፥
መቃብርን ‘አባቴ’ ብዬ እጠራዋለሁ፤ የሚበሉኝንም ትሎች ‘እናቴና እኅቴ’ እላቸዋለሁ።
እንደ ጣትህ ቀለበት ጠብቃቸው፤ በልብህም ሰሌዳ ቅረጻቸው።
እነርሱ ከአመንዝራ ሴት እንድትርቅና ከሌላ ሰው ሚስት አሳሳች ቃል እንድትጠበቅ ያደርጉሃል።
ምነው አንተ የእናቴን ጡት እንደ ጠባ እንደ ወንድሜ በሆንክልኝ፤ በመንገድ ላይ አግኝቼ ብስምህ ማንም ሰው አይንቀኝም ነበር፤