አበኔር ወደ ኬብሮን በደረሰ ጊዜ ኢዮአብ በግል ሊያነጋግረው የፈለገ በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ገለል አድርጎ ወሰደው፤ እዚያም ሆዱን ወግቶ ገደለው፤ ኢዮአብ ይህን ያደረገበት ምክንያት አበኔር ቀደም ብሎ ወንድሙን ዐሣሄልን ስለ ገደለበት ለመበቀል ነው።
ምሳሌ 7:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋ ለብዙ ሰዎች የመጥፊያ ምክንያት ሆናለች፤ እጅግ ብዙ ሰዎች በእርስዋ ተማርከው ጠፍተዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዋርዳ የጣለቻቸው ብዙ ናቸው፤ የገደለቻቸውም ስፍር ቍጥር የላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወግታ የጣለቻቸው ብዙ ናቸውና፥ እርሷም የገደለቻቸው እጅግ ብዙ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙዎችን ወግታ አስታለች፤ እርስዋም የገደለቻቸው ቍጥር የላቸውም። |
አበኔር ወደ ኬብሮን በደረሰ ጊዜ ኢዮአብ በግል ሊያነጋግረው የፈለገ በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ገለል አድርጎ ወሰደው፤ እዚያም ሆዱን ወግቶ ገደለው፤ ኢዮአብ ይህን ያደረገበት ምክንያት አበኔር ቀደም ብሎ ወንድሙን ዐሣሄልን ስለ ገደለበት ለመበቀል ነው።
እንዲህም አልኳቸው፦ “የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ኃጢአት የሠራው በእንደዚህ ያለ ጋብቻ አይደለምን? ከብዙ ሕዝቦች መካከል እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ አልነበረም። እግዚአብሔርም ወዶት በሕዝቡ በእስራኤል ላይ አነገሠው፤ እርሱ ግን በባዕዳን ሴቶች አማካይነት ኃጢአት ሠራ። በዚህ ዐይነቱ ኃጢአት ላይ ወደቀ፤
ከእነርሱ አንዳንዶቹ የዝሙት ኃጢአት እንደ ሠሩ እኛም የዝሙት ኃጢአት እንሥራ፤ እነርሱ ይህን በማድረጋቸው ከእነርሱ ኻያ ሦስት ሺህ ሰዎች በአንድ ቀን ሞተዋል።
እንደገና ወደ እናንተ ስመጣ አምላኬ ምናልባት በእናንተ ፊት ያዋርደኛል ብዬ እፈራለሁ፤ ከዚህ ቀደም ኃጢአት ሠርተው በዚሁ በሠሩት ርኲሰት፥ ዝሙትና፥ ስድነት ንስሓ ስላልገቡት ሰዎች ሐዘን ላይ እወድቃለሁ ብዬ እፈራለሁ።
ፍልስጥኤማውያንም ከማረኩት በኋላ ሁለቱን ዐይኖቹን አወጡ፤ ወደ ጋዛም ወስደው በነሐስ ሰንሰለት በማሰር በታሰረበት ቤት እህል እንዲፈጭ አደረጉት፤