እርስዋ ደፋርና ኀፍረተቢስ ሴት ነበረች፤ በቤትዋ መቀመጥ ስለማያስደስታት ዘወትር ትዞራለች፤
ጯኺና ማን አለብኝ ባይ ናት፤ እግሮቿ ዐርፈው ቤት አይቀመጡም፤
ሁከተኛና እንቢተኛ ናት፥ እግሮችዋም በቤትዋ አይቀመጡም፥
ሁከተኛና አበያ ናት፥ እግሮችዋም በቤቷ አያርፉም፥
እነርሱም “ሚስትህ ሣራ የት አለች?” አሉት። እርሱም “እዚያ ድንኳኑ ውስጥ ነች” አላቸው።
ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር ይልቅ በጣራ ማእዘን ላይ መኖር ይሻላል።
ዕውቀትን ማጣት፥ እንደ ለፍላፊ፥ ምንም ነገር እንደማታውቅ ደንቈሮና ኀፍረተቢስ ሴት መሆን ነው።
ጠንቃቆችና ንጹሖች፥ ደጎች፥ ለባሎቻቸውም የሚታዘዙ እንዲሆኑ ያስተምሩአቸው። ይህንንም የሚያደርጉት የእግዚአብሔር ቃል እንዳይነቀፍ ነው።