ምሳሌ 6:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንን ሳታደርግ አትተኛ፤ በዐይንህም እንቅልፍ አይዙር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐይኖችህ እንቅልፍ አይያዛቸው፣ ሽፋሽፍቶችህም አያንጐላጁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለዓይንህ እንቅልፍን ለሽፋሽፍቶችህም እንጉልቻን አትስጥ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዐይንህ እንቅልፍን፥ ለሽፋሽፍቶችህም ሸለብታን አትስጥ፤ |
ልጄ ሆይ! በዚያ ሰው ሥልጣን ሥር ሆነሃል ማለት ነው፤ ስለዚህ ከእርሱ ቊጥጥር ነጻ ለመውጣት ብትፈልግ ፈጥነህ ወደ እርሱ ሂድ፤ ዋስትናውንም እንዲያወርድልህ ለምነው።
አልፎ አልፎ የጌታ መልአክ ወደ ኲሬው ወርዶ ውሃውን ያናውጥ ነበር፤ ከውሃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ ወደ ኲሬው የሚገባ ካደረበት ከማንኛውም በሽታ ይፈወስ ነበር።]