ምሳሌ 31:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የበፍታ ልብስ እየሠራች ትሸጣለች፤ ለነጋዴዎችም ድግ ታስረክባለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የበፍታ መጐናጸፊያዎችን ሠርታ ትሸጣለች፤ ለነጋዴዎችም ድግ ታቀርባለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የበፍታ ልብስ እየሠራች ትሸጣለች፥ ለነጋዴም ድግ ትሸጣለች። |
የሶርያ ሕዝብ የንግድ ሸቀጥሽን ሁሉና ሌሎችንም ብዙ ዕቃዎች ይገዙሽ ነበር፤ በወሰዱአቸውም ዕቃዎች ምትክ በሉር፥ ሐምራዊና በጥልፍ ያጌጠ ልብስ፥ ቀጭን ሐር፥ ከዛጎል የተሠሩ ጌጣጌጦችና ቀይ ዕንቊ ይሰጡሽ ነበር፤
ሶምሶንም እንዲህ አላቸው፤ “እስቲ ታውቁ እንደ ሆነ አንድ እንቆቅልሽ ልንገራችሁ፤ በሰባቱ የሠርጉ በዓል ቀኖች ውስጥ ይህን እንቆቅልሽ ፈትታችሁ ብትነግሩኝ፥ ሠላሳ የበፍታ ቀሚስና ሠላሳ ቅያሬ ልብስ እሰጣችኋለሁ፤