ምሳሌ 27:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሎች ሰዎች ያመስግኑህ እንጂ ራስህን አታመስግን፤ ሰዎች ስለ አንተ ይመስክሩ እንጂ፥ አንተ ስለ ራስህ መልካምነት አትናገር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌላው ያመስግንህ እንጂ የገዛ አፍህ አይደለም፤ ሌላ ሰው ያወድስህ እንጂ የገዛ ከንፈርህ አይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌላ ያመስግንህ እንጂ ከአንተ አፍ አይውጣ፥ ባዕድ ሰው እንጂ ከንፈርህ አይሁን። |
ይሁን እንጂ ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንድ ሰዎች ጋር ራሳችንን ልናወዳድር ወይም ራሳችንን ልናነጻጽር አንደፍርም፤ እነርሱ ግን ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር በማመዛዘናቸውና ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር በማወዳደራቸው አስተዋዮች አይደሉም።
እንደ ሞኝ ተናገርኩ! ታዲያ፥ እንዲህ እንድናገር ያደረጋችሁኝ እናንተ ናችሁ፤ እኔን ማመስገን የሚገባችሁ እናንተ ነበራችሁ፤ እኔ ማንነቴ ያልታወቀ ሰው ብሆንም እንኳ ታላላቅ ከተባሉት ሐዋርያት በምንም አላንስም።