ምሳሌ 27:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነፋስን ለማቆም ዘይትንም በእጅ ጨብጦ ለመያዝ እንደማይቻል ሁሉ እርስዋንም ዝም ማሰኘት አይቻልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷን ለመግታት መሞከር፣ ነፋስን እንደ መግታት ወይም ዘይትን በእጅ እንደ መጨበጥ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷንም መከልከል ነፍስን መከልከልና ዘይትን በቀኝ እጅ መጨበጥ ነው። |
በዚያን ጊዜ ማርያም ዋጋው እጅግ የከበረ ከንጹሕ ናርዶስ የተሠራ፥ ግማሽ ሊትር የሚሆን አንድ ብልቃጥ ሽቶ ወስዳ፥ የኢየሱስን እግሮች ቀባች፤ በጠጒርዋም አበሰቻቸው፤ ቤቱም በሽቶው መዓዛ ተሞላ።