15 ተጨቃጫቂ ሚስት እንደማያቋርጥ ዝናብ አሰልቺ ናት፤
15 ጨቅጫቃ ሚስት፣ በዝናብ ቀን እንደሚወርድ የማያቋርጥ ጠፈጠፍ ናት፤
15 በዝናብ ቀን የሚያንጠባጥብ ቤትና ጠበኛ ሴት አንድ ናቸው፥
ሞኝ ልጅ አባቱን ወደ ጥፋት ያደርሳል፤ ጨቅጫቃ ሚስትም እንደማያቋርጥ ዝናብ አሰልቺ ናት።
ከጨቅጫቃና ከነዝናዛ ሚስት ጋር አብሮ ከመኖር በምድረ በዳ መኖር ይሻላል።
ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር ይልቅ በጣራ ማእዘን ላይ መኖር ይሻላል።
ውሃ ድንጋይን እየቦረቦረ እንደሚጨርስ፥ ኀይለኛ ዝናብም መሬትን እንደሚሸረሽር፥ አንተም እንዲሁ የደካማን ሰው ተስፋ ታጠፋለህ።
ነፋስን ለማቆም ዘይትንም በእጅ ጨብጦ ለመያዝ እንደማይቻል ሁሉ እርስዋንም ዝም ማሰኘት አይቻልም።