ምሳሌ 26:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆኖም ጠቢብ ነኝ ብሎ እንዳይመጣ ሞኝነቱን በመግለጥ መልስለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞኝን እንደ ቂልነቱ መልስለት፤ አለዚያ ጠቢብ የሆነ ይመስለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለራሱ ጠቢብ የሆነ እንዳይመስለው ለሞኝ እንደ ሞኝነቱ መልስለት። |
ወንድሞቼ ሆይ! “ዐዋቂዎች ነን” ብላችሁ አትመኩ፤ የምነግራችሁ አንድ ምሥጢር አለ፤ ይኸውም የእስራኤላውያን እምቢተኛነት ለዘለቄታው ሳይሆን አሕዛብ ሁሉ በሙላት ወደ እግዚአብሔር እስኪመጡ ድረስ መሆኑን ነው።
እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማምታችሁ ኑሩ፤ ራሳችሁን ከፍ ከማድረግ ይልቅ ትዕቢትን አስወግዳችሁ ከድኾች ጋር በአንድነት ኑሩ፤ በራሳችሁ ዐዋቂዎች ነን አትበሉ።