መዝጊያ በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር ሰነፍም በአልጋው ላይ መገላበጥ ያበዛል።
መዝጊያ በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፣ ሰነፍም በዐልጋው ላይ ይገላበጣል።
መዝጊያ በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፥ እንዲሁ ሰነፍ ሰው በአልጋው ላይ ይገላበጣል።
በሥራ ትጉህ መሆን ገዢ ያደርጋል፤ ሰነፍ መሆን ግን ተገዢ ያደርጋል።
ሰነፍ ከሆንክ የምትመኘውን ማግኘት አትችልም፤ በትጋት ከሠራህ ግን ትበለጽጋለህ።
ብትፈልግ ትንሽ ሸለብ ያድርግህ፤ ጥቂት እንቅልፍም ይውሰድህ፤ እጆችህንም አጣምረህ ለጥቂት ጊዜ ዐረፍ በል።
አንተ ሰነፍ ወደ ጒንዳን ሄደህ መንገድዋን ተመልክተህ ጥበብን ቅሰም።
የምንመኘውም በእምነትና በትዕግሥት ጸንተው ተስፋ የተሰጣቸውን ነገር የሚወርሱትን ሰዎች እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንድትሆኑ አይደለም።