ሰነፍ ሰው “አንበሳ በመንገድ ላይ አለ፤ የሚያስፈሩ አንበሶች በጐዳናዎች ይዘዋወራሉ” ይላል።
ሰነፍ፣ “በመንገድ ላይ አንበሳ አለ፤ አስፈሪ አንበሳ በጐዳና ላይ ይጐማለላል” ይላል።
ሰነፍ ሰው፦ “አንበሳ በመንገድ ላይ አለ፥ አንበሳ በጎዳናዎች ላይ አለ” ይላል።
የሰነፍ መንገድ በችግር እሾኽ የታጠረ ነው፤ የቅን ሰው መንገድ ግን እንደ ተስተካከለ ጐዳና ነው።
ስንፍና እንቅልፍን ያስከትላል፤ ስለዚህም ሰነፍ ሰው ይራባል።
ሰነፍ ሰው “ውጪ አንበሳ አለ፤ ብወጣ ይገድለኛል” ብሎ ይከራከራል። “አንበሳ ያገኘኛል” በማለት ከቤቱ አይወጣም።
አንተ ሰነፍ ወደ ጒንዳን ሄደህ መንገድዋን ተመልክተህ ጥበብን ቅሰም።
ስለዚህ ፈራሁና ሄጄ ገንዘብህን በመሬት ውስጥ ቀበርኩት፤ ይኸውልህ ገንዘብህ!’ አለው።