በሰነፍና ማስተዋል በጐደለው ሰው እርሻ ውስጥ በወይኑም አትክልት ቦታ ሄድኩኝ፤
በሰነፍ ሰው ዕርሻ በኩል ዐለፍሁ፤ በልበ ቢስ ሰው የወይን ቦታ ዐልፌ ሄድሁ፤
በሰነፍ ሰው እርሻ፥ አእምሮ በጐደለውም ሰው ወይን ቦታ አለፍሁ።
እግዚአብሔር ጥበብን አስተማረኝ፥ የቅዱሳንንም ዕውቀት ዐወቅሁ።
“አባቶቻቸው ሳይደብቁ ያስተላልፉላቸውን፥ ጥበበኞች የገለጡትን፥ እኔም የመረመርኩትን አስረዳሃለሁና ስማኝ፤ ልንገርህ።
እኔ እንዳስተዋልኩት ክፋትን የሚያርሱና መከራን የሚዘሩ ያንኑ ይሰበስባሉ።
እኛ ይህን ሁሉ መርምረን እውነት መሆኑን ዐውቀናል አንተም አስተውለህ ተግባራዊ አድርገው።”
ቅኖች ይህን በማየት ደስ ይላቸዋል፤ ክፉዎች ግን ዐፍረው ዝም ይላሉ።
ከወጣትነት እስከ ሽምግልና ኖሬአለሁ፤ ታዲያ፥ እግዚአብሔር ደጉን ሰው ሲተወው፥ ልጆቹም ምግብ አጥተው ሲለምኑ፥ ከቶ አይቼ አላውቅም።
በአእምሮ የበሰሉ ሰዎች በማስተዋል ይናገራሉ። ሞኞች ግን ቅጣት መቀበል የሚገባቸው ናቸው።
ትጉህ ገበሬ የተትረፈረፈ ምግብ ይኖረዋል፤ በከንቱ ምኞት መጠመድ ግን ሞኝነት ነው።
ሰነፍ አንድ ነገር ለማግኘት አጥብቆ ይመኛል፤ ይሁን እንጂ አያገኝም፤ ትጉህ ሠራተኛ ግን የሚፈልገውን ሁሉ ያገኛል።
የምንዝር ተግባር የሚፈጽም ሰው ግን ማስተዋል የጐደለው ነው፤ ሕይወቱንም በከንቱ ያጠፋል።
ሰው ቤቱን ከመጠገን ቸል ቢል ጣራው ይዘብጣል፤ ክዳኑም ያፈሳል።
ከንቱ በሆነው ዘመኔ ክፉ ሰው በሚሠራው በደል እስከ ረጅም ዕድሜ ሲኖር፥ ደግ ሰው ግን በደግነቱ ሲጠፋ ብዙ ነገር አይቼበታለሁ፤