በዚህ ነገር ደስ ቢልህ ግን እግዚአብሔርን ታሳዝናለህ፤ እግዚአብሔርም በጠላትህ ላይ የሚያሳየውን ቊጣ ያቆማል።
አለዚያ እግዚአብሔር ይህን አይቶ ደስ አይለውም፤ ቍጣውንም ከርሱ ይመልሳል።
ጌታ ይህንን አይቶ እንዳያዝንብህ፥ ቁጣውንም ከእርሱ ላይ እንዳያነሣ።
እግዚአብሔር ያያልና፥ ደስም አያሰኘውምና፥ ቍጣውን ከእርሱ ይመልሳል።
ጠላትህ ሲሰናከል ደስ አይበልህ፤ በሚወድቅበትም ጊዜ ሐሤት አታድርግ፤
በክፉ ሰዎች አድራጎት አትጨነቅ፤ በእነርሱም አትቅና፤