ምሳሌ 24:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በግፍ ወደ ሞት የሚወሰዱትን ሰዎች ታደግ፤ ለመገደል እያዳፉ ከሚወስዱአቸው ሰዎች እጅ አድን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ሞት የሚነዱትን ታደጋቸው፤ እየተጐተቱ ለዕርድ የሚሄዱትን አድናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ሞት የሚነዱትን ታደግ፥ ለመታረድ የተወሰነባቸውን አድን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሞት የሚነዱትን ታደግ፤ የሚገደሉትንም መዋረዳቸውን ቸል አትበል። |
ጠቡ እየከረረ ስለ ሄደ ሰዎቹ ጳውሎስን እንዳይቦጫጭቁት ፈርቶ አዛዡ “ውረዱና ጳውሎስን ከሰዎቹ መካከል ነጥቃችሁ አምጡ! ወደ ጦሩ ሰፈርም ውሰዱት!” በማለት ወታደሮቹን አዘዘ።