ምሳሌ 21:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሐሰተኛ ሰው ምስክርነት ውድቅ ይሆናል፤ በጥንቃቄ አስቦ የሚናገር ሰው ቃል ግን ይጸናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፤ እውነቱን የሚናገር ግን ጸንቶ ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፥ የሚሰማ ሰው ግን ተጠንቅቆ ይናገራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፤ የሚሰማ ሰው ግን ተጠንቅቆ ይናገራል። |
እነርሱም “አብደሻል!” አሉአት። እርስዋ ግን “በእውነት እርሱ ነው!” ስትል አረጋገጠች፤ እነርሱም እንግዲያውስ “የእርሱ ጠባቂ መልአክ ይሆናል” አሉ።
ይሁን እንጂ “አመንኩ፤ ስለዚህ ተናገርኩ” ተብሎ እንደ ተጻፈው፥ እኛም ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን እናምናለን፤ ስለዚህም እንናገራለን።
ይህ የታመነ አባባል ነው። በእግዚአብሔር ያመኑ ሰዎች ለመልካም ሥራ እንዲተጉ ይህን ነገር ሁሉ በጥብቅ እንድታስገነዝብ እፈልጋለሁ፤ ይህም ነገር መልካምና ለእያንዳንዱ ሰው ጠቃሚ ነው።