የበደለን ሰው ይቅር የሚል ወዳጅነትን ያጸናል፤ በደልን መላልሶ የሚናገር ሰው ግን የቅርብ ወዳጆቹን ያጣል።
በደልን የሚሸፍን ፍቅርን ያዳብራል፤ ነገርን የሚደጋግም ግን የልብ ወዳጆችን ይለያያል።
ኃጢአትን የሚከድን ሰው ፍቅርን ይሻል፥ ነገርን የሚደጋግም ግን የተማመኑትን ወዳጆቹን ይለያያል።
በደሉን የሚሰውር ሰው ዕርቅን ይሻል፤ በደሉን መሰወር የሚጠላ ግን ቤተሰቦችንና ወዳጆችን ይለያያል።
ኃጢአታቸው ይቅር የተባለላቸውና በደላቸውም የተሰረየላቸው ሰዎች የተባረኩ ናቸው።
ጥላቻ ሁከትን ያነሣሣል፤ ፍቅር ግን በደልን ሁሉ አይታ በይቅርታ ታልፋለች።
ተንኰለኛ ሰው ጠብን ይዘራል፤ ሐሜተኛም የቅርብ ወዳጆችን እንዲለያዩ ያደርጋል።
ሞኝ መቶ ጊዜ ተገርፎ ከሚማረው ይልቅ አስተዋይ ሰው ከአንድ ጊዜ በማይበልጥ ተግሣጽ የሚማረው ይበልጣል።
ፍቅር ያስታግሣል፤ ፍቅር ደግ ያደርጋል፤ ፍቅር ቀናተኛ አያደርግም፤ ፍቅር ያለው ሰው አይመካም፤ ፍቅር ያለው ሰው አይታበይም፤
ኃጢአተኛውን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልስ፥ የኃጢአተኛውን ነፍስ ከሞት እንደሚያድንና የብዙ ኃጢአቱንም ይቅርታ እንደሚያስገኝለት ይወቅ።
ፍቅር ብዙ ኃጢአትን ስለሚሸፍን ከሁሉ በላይ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።