ጠማማ ልብ ያለው አይበለጽግም፤ አንደበቱ አታላይ የሆነ ሰው ችግር ላይ ይወድቃል።
ጠማማ ልብ ያለው ሰው አይሳካለትም፤ በአንደበቱ የሚቀላምድም መከራ ላይ ይወድቃል።
ጠማማ ልብ ያለው መልካምን አያገኝም፥ ምላሱንም የሚገለብጥ በክፉ ላይ ይወድቃል።
ጠማማ ልብ ያለው መልካም ነገርን አያገኝም፥ አንደበቱን የሚለዋውጥም በክፉ ላይ ይወድቃል።
ለንጹሖች ንጹሕ ነህ፤ ለጠማሞች ግን ተገቢ ዋጋቸውን ትሰጣለህ።
በሰው ላይ መጠቃቀስ ችግርን ያመጣል፤ በግልጥ የሚነቅፍ ግን ሰላም እንዲገኝ ያደርጋል።
ጠቢባን በሚቻላቸው ዘዴ ሁሉ ዕውቀትን ያከማቻሉ፤ ሞኞች በሚናገሩበት ጊዜ ግን ጥፋት መምጣቱ አይቀርም።
ደጋግ ሰዎች ጥበብን ይናገራሉ፤ ጠማማ ነገር የምትናገር ምላስ ግን ትቈረጣለች።
ዐመፀኛ ሰው “ወደ ፊት ይህን አገኛለሁ” ብሎ ተስፋ የሚያደርገው ነገር የለውም።
እግዚአብሔር ክፉ አድራጊዎችን ይጠላል፤ ልበ ቅኖችን ግን አጥብቆ ይወዳቸዋል።
ክፉ ነገርን መጥላት እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ እኔ ትዕቢትንና ዕብሪትን እጠላለሁ፤ ክፉ መንገድንና ጠማማ ንግግርን አልወድም
ጥበበኛ ሰው በንግግሩ ክብርን ያገኛል፤ ሞኝ ግን በገዛ ንግግሩ ይጠፋል፤