ምሳሌ 16:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጥበበኛ ሰው አእምሮ ንግግሩን ይቈጣጠራል፤ ከአፉም የሚወጣው ንግግር ትምህርትን ያስፋፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጠቢብ ሰው ልብ አንደበቱን ይመራል፤ ከንፈሮቹም ዕውቀትን ያዳብራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጠቢብ ልብ አፉን ያስተምራል፥ ለከንፈሩም ትምህርትን ይጨምራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጠቢብ ልብ ከአፉ ይታወቃል፥ በከንፈሩም ዕውቀትን ይለብሳል። |
የክርስቶስ ቃል በሙላት በልባችሁ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ።