ነገሥታት በእውነተኛ ንግግር ይደሰታሉ፤ እውነት የሚናገረውንም ሰው ያከብራሉ።
ነገሥታት በታማኝ ከንፈሮች ደስ ይላቸዋል፤ ጽድቅ የሚናገረውን ሰው ይወድዱታል።
የጽድቅ ከንፈር የነገሥታት ደስታ ናት፥ በቅን የሚናገር እርሱንም ይወድዱታል።
የእውነት ከንፈር በንጉሥ ዘንድ የተወደደ ነው፥ ቅን ነገርንም ይወድዳል።
ነገሥታት ችሎታ ባላቸው አገልጋዮች ይደሰታሉ፤ አሳፋሪ አገልጋዮች ግን ንጉሡን ያስቈጣሉ።
መንግሥት የሚጸናው በፍትሕ ስለ ሆነ ክፉ ሥራ በመሪዎች ዘንድ የተጠላ ነው።
የንጉሥ ቊጣ የሞት መልእክተኛ ነው። ብልኅ ሰው ግን ቊጣውን ያበርዳል።
የልብ ንጽሕናንና መልካም ንግግርን የሚወድ ሰው በንጉሥ ዘንድ የተወደደ ይሆናል።