ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ለሰሎሞንም እንዲህ አለ፤ “አይዞህ በርታ ሥራውንም በቶሎ ጀምር፤ ምንም ነገር አይግታህ፤ እኔ የማገለግለው እግዚአብሔር አምላክ ከአንተ ጋር ነው፤ ለቤተ መቅደሱ ሥራ ያለህን አገልግሎት እስክትፈጽም ድረስ ከአንተ አይለይም፤ አይተውህም፤ ከቶም አይጥልህም፤
ምሳሌ 15:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞኝ የአባቱን ምክር ይንቃል፤ ተግሣጽን የሚቀበል ግን አስተዋይ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቂል የአባቱን ምክር ይንቃል፤ መታረምን የሚቀበል ግን አስተዋይነቱን ያሳያል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰነፍ የአባቱን ተግሣጽ ይንቃል፥ ዘለፋን የሚቀበል ግን አእምሮው የበዛ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አላዋቂ ልጅ የአባቱን ተግሥጽ ያቃልላል፤ ተግሣጽን የሚጠብቅ ግን ዐዋቂ ነው። እውነት ከበዛ ዘንድ ብዙ ኀይል አለ፥ ኀጢአተኞች ግን ከምድር ገጽ ይጠፋሉ፥ |
ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ለሰሎሞንም እንዲህ አለ፤ “አይዞህ በርታ ሥራውንም በቶሎ ጀምር፤ ምንም ነገር አይግታህ፤ እኔ የማገለግለው እግዚአብሔር አምላክ ከአንተ ጋር ነው፤ ለቤተ መቅደሱ ሥራ ያለህን አገልግሎት እስክትፈጽም ድረስ ከአንተ አይለይም፤ አይተውህም፤ ከቶም አይጥልህም፤
ዳዊት ሰሎሞንንም እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፥ የአባትህን አምላክ እንድታውቅ፥ በሙሉ ልብና በፈቃደኛ አእምሮ እንድታገለግለው ዐደራ እልሃለሁ፤ እርሱ ሐሳባችንንና ምኞታችንን ሁሉ ያውቃል፤ ወደ እርሱ ብትቀርብ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል፤ ብትተወው ግን እርሱም ለዘለዓለም ይተውሃል፤
ደግ ሰው በቅንነት መንፈስ ሊቀጣኝና ሊገሥጸኝ ይችላል፤ ከክፉ ሰዎች ግን ክብርን እንኳ አልቀበልም፤ ዘወትርም ክፉ ሥራቸውን በመቃወም እጸልያለሁ።