ምሳሌ 15:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀብታም ሆኖ በሁከት ከመኖር ድኻ ሆኖ እግዚአብሔርን በማክበር መኖር ይሻላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋራ ያለ ጥቂት ነገር፣ ሁከት ካለበት ትልቅ ሀብት ይበልጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታን ከመፍራት ጋር ያለ ጥቂት ነገር ሁከት ካለበት ከብዙ መዝገብ ይሻላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን በመፍራት የሚገኝ ጥቂት ሀብት እግዚአብሔርን ባለመፍራት ከሚገኝ ብዙ መዝገብ ይሻላል። |
“ያለኝ ይበቃኛል” ለሚል ሰው እግዚአብሔርን ማምለክ ትልቅ ጥቅም ያስገኝለታል። መንፈሳዊነትን ስለሚያተርፍበት ሃይማኖት የሀብት ምንጭ ነው።