6 ሀብታም ሆኖ አታላይ ከመሆን ይልቅ ድኻ ሆኖ ታማኝ መሆን ይሻላል።
6 በአካሄዱ ነውር የሌለበት ድኻ፣ መንገዱ ጠማማ ከሆነ ባለጠጋ ይሻላል።
6 በጠማማ መንገድ ከሚሄድ ሀብታም ያለ ነውር የሚሄድ ድሀ ይሻላል።
አካሄዱ ቀጥተኛ የሆነ ሰው እግዚአብሔርን ይፈራል፤ መንገዱ ጠማማ የሆነ ሰው ግን እግዚአብሔርን አይፈራም።
ፍትሕን በማጓደል ከሚገኝ ብዙ ሀብት ይልቅ በእውነት የሚገኝ ጥቂት ነገር ይሻላል።
በንግግሩ ከሚቀላምድ ሞኝ ሰው ይልቅ በቅንነት የሚኖር ድኻ ሰው ይሻላል።
ከሰው የሚፈለገው ታማኝነት ነው፤ ሐሰተኛ ከመሆን ይልቅ ድኻ መሆን ይሻላል።
ታማኝ ሰው በሰላም ይኖራል፤ ጠማማ ሰው ግን በጒድጓድ ውስጥ ይወድቃል።