ምሳሌ 12:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀብታም መስሎ በችግር ከሚኖር ሰው ይልቅ፥ ተራ ሰው መስሎ እየሠራ ኑሮውን የሚያሸንፍ ይሻላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚበላው ሳይኖረው ከሚኵራራ ይልቅ፣ ራሱን ዝቅ አድርጎ ሠራተኛ የሚያሳድር ይሻላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምግብ ሳይኖረው ከሚኮራ ሰው አገልጋይ ኖሮት የተዋረደ ሰው ይሻላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለራሱ ባሪያ ሆኖ የተጠቃ ሰው እንጀራ ጐድሎት ራሱን ካከበረው ሰው ይሻላል። |
አንዳንድ ሰዎች ምንም ሳይኖራቸው ሀብታም መስለው ለመታየት ይጥራሉ፤ ሌሎች ደግሞ ብዙ ሀብት እያላቸው፥ ምንም ሀብት እንደሌላቸው መስለው ይኖራሉ።