ምሳሌ 12:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ሰው በክፋት ጸንቶ ሊቆም አይችልም። የእውነተኞች ሰዎች መሠረት ግን አይናወጥም አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው በክፋት ላይ ተመሥርቶ ሊጸና አይችልም፤ ጻድቃን ግን ከቦታቸው አይነቃነቁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፋት ለሰው ዋስትና አያስገኝም፥ የጻድቃንን ሥር ግን ምንም አያንቀሳቅሰውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዐመፃ የማይርቅ ሰው ይጠፋል፤ የጻድቃን ሥር ግን አይነቀልም። |
ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ ንጹሕ ሰዎችን ለመጒዳት ጉቦ የማይቀበል፥ እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ከቶ አይናወጥም። በሰላም ይኖራል እንጂ ከቶ አይናወጥም።
የሕይወትን እስትንፋስ ለማስቀረትና የሞትን ቀን ለመለወጥ የሚችል ማንም የለም፤ ማንም ሰው ከጦር ሜዳ መሰናበት እንደማይችል ክፋትም ክፉ ሠሪዎችን አይለቃቸውም።