እነርሱም ምንቸቶችንና የሸክላ ማሰሮዎችን፥ የመኝታ አልጋዎችንም ይዘው መጡ፤ እንዲሁም ለዳዊትና ለተከታዮቹ የሚሆን ስንዴ፥ ገብስ፥ ዱቄት፥ የተጠበሰ እሸት፥ ባቄላ፥ አተር፥ ማር፥ አይብ፥ እርጎና በጎችን አመጡ፤ ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት ዳዊትና ተከታዮቹ በበረሓ ኑሮ እንደሚርባቸው፥ እንደሚጠማቸውና እንደሚደክማቸው በማሰብ ነው።
ምሳሌ 11:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለጋስ ሁን፤ ትበለጽጋለህ፤ ሌሎችን እርዳ፤ አንተም ርዳታ ታገኛለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለጋስ ይበለጽጋል፤ ሌሎችን የሚያረካም ራሱ ይረካል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በረከትን የምታካፍል ነፍስ ትጠግባለች፥ ውሃን የሚያጠጣ እርሱ ደግሞ ይረካል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተባረከች ሰውነት ሁሉ ትጠግባለች፥ ቍጡ ሰው ግን ክፉ ነው። |
እነርሱም ምንቸቶችንና የሸክላ ማሰሮዎችን፥ የመኝታ አልጋዎችንም ይዘው መጡ፤ እንዲሁም ለዳዊትና ለተከታዮቹ የሚሆን ስንዴ፥ ገብስ፥ ዱቄት፥ የተጠበሰ እሸት፥ ባቄላ፥ አተር፥ ማር፥ አይብ፥ እርጎና በጎችን አመጡ፤ ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት ዳዊትና ተከታዮቹ በበረሓ ኑሮ እንደሚርባቸው፥ እንደሚጠማቸውና እንደሚደክማቸው በማሰብ ነው።
አንዳንድ ሰዎች በለጋሥነት ገንዘባቸውን ይበትናሉ፤ ነገር ግን ሀብታቸው እየበዛ ይሄዳል፤ ሌሎች ደግሞ ያለ ልክ ለገንዘባቸው ይሳሳሉ፤ ነገር ግን ድኽነታቸው እየበዛ ይሄዳል።