ምሳሌ 11:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በሐሰተኛ ሚዛን የሚያታልሉትን ሰዎች ይጠላል፤ በትክክለኛ ሚዛን በሚመዝኑት ሰዎች ግን ይደሰታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የተጭበረበረ ሚዛንን ይጸየፋል፤ ትክክለኛ መለኪያ ግን ደስ ያሠኘዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሐሰት ሚዛን በጌታ ፊት አስጸያፊ ነው፥ እውነተኛ ሚዛን ግን ደስ ያሰኘዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባይ ሚዛን በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው፤ እውነተኛ ሚዛን ግን በእርሱ ዘንድ የተመረጠ ነው። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስራኤላውያን ሐሰተኛ ሚዛን በእጃቸው እንደሚገኝ እንደ ከነዓናውያን ነጋዴዎች ሆነዋል፤ በእርሱም ያታልሉበታል፤