ምሳሌ 10:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደጋግ ሰዎች የሚፈልጉትን ያገኛሉ፤ ክፉዎች ግን እጅግ የፈሩት ነገር ይደርስባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ ሰው የፈራው ይደርስበታል፤ ጻድቅ የሚመኘው ይፈጸምለታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የክፉ ሰው ፍርሃት በላዩ ይመጣበታል፥ ለጻድቃንም ምኞታቸው ትሰጣቸዋለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኃጥእ ወደ ጥፋት ይመለሳል፥ የጻድቅ ምኞቱ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደች ናት። |
ስጠራ ማንም ስላልመለሰልኝ፥ ስናገር ማንም ስላላዳመጠኝ ነገር በፊቴ ክፉ የሆነውን ነገር ስላደረጉና የማያስደስተኝን ስለ መረጡ እኔም በእነርሱ ላይ ቅጣት አመጣባቸዋለሁ።”