ምሳሌ 10:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስሕተት በማድረግ መደሰት ሞኝነት ነው፤ በአእምሮ የበሰሉ ሰዎች ደስ የሚላቸው ጥበብን በማግኘት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞኝ ሰው በክፉ ተግባር ይደሰታል፤ አስተዋይ ሰው ግን በጥበብ ደስ ይለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ ነገር ማድረግ ለአላዋቂ ጨዋታ ነው፥ እንዲሁም ጥበብ ለአስተዋይ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰነፍ ሰው በመሳቁ ክፉን ይሠራል፤ ጥበብ ግን ለሰው ዕውቀትን ትወልዳለች። |
ወጣት ሆይ! ወጣትነት እጅግ ግሩም ስለ ሆነ በወጣትነትህ ዘመን ደስ ይበልህ፤ በልብህም ሐሤት አድርግ፤ ዐይንህ የሚያየውንና ልብህ የሚመኘውን ሁሉ ፈጽም፤ ሆኖም ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።