ነቢዩ ገና ንግግሩን ሳይፈጽም አሜስያስ “ለመሆኑ አንተን የንጉሡ አማካሪ አድርገን የሾምንህ ከመቼ ወዲህ ነው? ይልቅስ ንግግርህን አቁም፤ አለበለዚያ እገድልሃለሁ!” አለው። ነቢዩም ለአንድ አፍታ ንግግሩን ቆም ካደረገ በኋላ “ይህን ሁሉ በማድረግህና የእኔን ምክር ለመስማት እምቢ በማለትህ እግዚአብሔር ሊያጠፋህ መወሰኑን አሁን ዐወቅሁ” አለው።
ምሳሌ 10:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተግሣጽን የሚቀበሉ ሰዎች ወደ ሕይወት መንገድ ያመራሉ፤ ከስሕተታቸው የማይማሩ ሰዎች ግን አደጋ ላይ ይወድቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተግሣጽን ነቅቶ የሚጠብቅ የሕይወትን መንገድ ያሳያል፤ ዕርምትን የማይቀበል ግን ሌሎችን ወደ ስሕተት ይመራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተግሣጽን የሚጠብቅ በሕይወት መንገድ ይሄዳል፥ ዘለፋን የሚተው ግን ይስታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተግሣጽ የሕይወትን መንገድ ይጠብቃታል፤ በተግሣጽ የማይዘለፍ ግን ይስታል። |
ነቢዩ ገና ንግግሩን ሳይፈጽም አሜስያስ “ለመሆኑ አንተን የንጉሡ አማካሪ አድርገን የሾምንህ ከመቼ ወዲህ ነው? ይልቅስ ንግግርህን አቁም፤ አለበለዚያ እገድልሃለሁ!” አለው። ነቢዩም ለአንድ አፍታ ንግግሩን ቆም ካደረገ በኋላ “ይህን ሁሉ በማድረግህና የእኔን ምክር ለመስማት እምቢ በማለትህ እግዚአብሔር ሊያጠፋህ መወሰኑን አሁን ዐወቅሁ” አለው።
ወደ ኃጢአት እንዳይመራህ ለአንደበትህ ከገደብ ያለፈ ነጻነት አትስጠው፤ በዚህ ዐይነት “ይህን የተናገርኩት ሳላውቅ ነው” ብለህ በእግዚአብሔር አገልጋይ ፊት ይቅርታ ከመጠየቅ ትድናለህ፤ አለበለዚያ ግን የደከምክበትን ያጠፋ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቊጣ በገዛ እጅህ እንደ መጋበዝ ይሆንብሃል።
ያንን የሚናገረውን አንቀበልም እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ እግዚአብሔር በሰው አማካይነት ከምድር ሲናገራቸው አንሰማም ያሉት ካላመለጡ፥ ታዲያ እኛ ከሰማይ የሚናገረንን ባንቀበል እንዴት እናመልጣለን!