ምሳሌ 10:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደግ ሰው መልካም ሥራ ሕይወትን ያስገኝለታል፤ የክፉ ሰው ኃጢአት ግን ቅጣትን ያስከትልበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጻድቃን ደመወዝ ሕይወት ታስገኝላቸዋለች፤ የክፉዎች ትርፍ ግን ቅጣትን ታመጣባቸዋለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጻድቅ ደመወዝ ለሕይወት ነው፥ የክፉ ገቢው ግን ለኃጢአት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጻድቃን ሥራ ሕይወትን ያደርጋል፤ የኃጥኣን ፍሬ ግን ኀጢአት ነው። |
ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ እግዚአብሔር አብ የማረጋገጫ ማኅተም ስለ አተመው የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ፥ የዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው ምግብ ሥሩ።”
ከኃጢአት የሚገኘው ዋጋ ሞት ነው፤ ከእግዚአብሔር የሚሰጠው ስጦታ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሚገኘው የዘለዓለም ሕይወት ነው።
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ፤ ለጌታ ሥራ የምትደክሙት በከንቱ አለመሆኑን ዐውቃችሁ፥ ሳታቋርጡ ዘወትር የጌታን ሥራ ለመሥራት ትጉ።