ምሳሌ 10:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ የሰሎሞን ምሳሌዎች ናቸው፤ ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሞኝ ልጅ ግን ለእናቱ ሐዘንን ያተርፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰሎሞን ምሳሌዎች፤ ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሞኝ ልጅ ግን ለእናቱ ሐዘንን ያተርፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰሎሞን ምሳሌዎች። ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፥ አላዋቂ ልጅ ግን ለእናቱ ኀዘን ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሰነፍ ልጅ ግን እናቱን ያሳዝናታል። |
እነዚህ ሌሎች የሰሎሞን ምሳሌዎች ናቸው፤ እነርሱም በእጅ የተጻፉት በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ቤተ መንግሥት በነበሩ ሰዎች አማካይነት ነበር።
ከእኔ በኋላ የሚመጣው ጠቢብ ይሁን ሞኝ ተለይቶ አይታወቅም፤ ይሁን እንጂ እኔ የደከምኩበትንና በጥበቤ ያተረፍኩትን ነገር ሁሉ ወስዶ ባለቤት ይሆናል፤ ይህም ከንቱ ነው።