ፊልሞና 1:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የክርስቶስ በመሆናችን ያለን መልካም ነገር ሁሉ በይፋ ይታወቅ ዘንድ እምነትህን ለሌሎች ለማካፈል እንድትተጋ እጸልያለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በክርስቶስ ስላለን መልካም ነገር ሁሉ በሚገባ ትረዳ ዘንድ፣ እምነትህን ለሌሎች በማካፈል እንድትተጋ እጸልያለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእምነትህም ኅብረት፥ በእኛ ዘንድ ያለውን በጎ ነገር ሁሉ በማወቅ፥ ለክርስቶስ ኢየሱስ ፍሬ እንዲያፈራ እለምናለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእምነትህም ኅብረት፥ በእኛ ዘንድ ያለውን በጎ ነገር ሁሉ በማወቅ፥ ለክርስቶስ ኢየሱስ ፍሬ እንዲያፈራ እለምናለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእምነትህም ኅብረት፥ በእኛ ዘንድ ያለውን በጎ ነገር ሁሉ በማወቅ፥ ለክርስቶስ ኢየሱስ ፍሬ እንዲያፈራ እለምናለሁ፤ |
አእምሮአችሁ በእነዚህ ከሁሉ በሚበልጡና በሚያስመሰግኑ መልካም ነገሮች የተመላ ይሁን፤ በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ! እውነተኛ፥ ክቡር፥ ትክክለኛ፥ ንጹሕ፥ አስደሳችና ምስጉን የሆኑ ነገሮችን ሁሉ አስቡ።
ስለዚህ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምሮ እናንተ በመንፈሳዊ ጥበብና ማስተዋል ሁሉ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምትገነዘቡበት ሙሉ ዕውቀት እንዲኖራችሁ ለእናንተ ከመጸለይና እግዚአብሔርን ከመለመን አላቋረጥንም።
ምናልባት “ክፉ አድራጊዎች ናቸው” ብለው ቢያሙአችሁም እንኳ እግዚአብሔር እኛን ለመጐብኘት በሚመጣበት ቀን አሕዛብ መልካም ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ በእነርሱ መካከል ስትኖሩ መልካም ጠባይ ይኑራችሁ።
እንዲሁም እናንተ ሚስቶች! ለባሎቻችሁ ታዘዙ፤ በዚህ ዐይነት አንዳንዶች በእግዚአብሔር ቃል የማያምኑ ቢሆኑም እንኳ ያለ ቃሉ ትምህርት በሚስቶቻቸው ጠባይ ብቻ ሊሳቡ ይችሉ ይሆናል።
መልሳችሁ ግን በገርነትና በአክብሮት ይሁን፤ የክርስቶስ በመሆናችሁ ባላችሁ መልካም ጠባይ ላይ ክፉ የሚናገሩ ሰዎች በክፉ ንግግራቸው እንዲያፍሩ መልካም ኅሊና ይኑራችሁ።