ይህንማ ያቀደው የሠራዊት አምላክ ነው፤ እርሱም ይህን ያቀደው ባደረጉት ነገር መታበያቸውን እንዲተዉ ለማድረግና የተከበሩትንም ሰዎች ለማዋረድ ብሎ ነው።
አብድዩ 1:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ኤዶምን እንዲህ ይላል፦ “እነሆ በአሕዛብ መካከል ደካማ አደርግሃለሁ፤ እጅግም የተናቅህ ትሆናለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እነሆ፤ በአሕዛብ መካከል ታናሽ አደርግሃለሁ፤ እጅግ የተናቅህ ትሆናለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ በአሕዛብ ዘንድ ታናሽ አድርጌሃለሁ፥ አንተ እጅግ ተንቀሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ በአሕዛብ ዘንድ ታናሽ አድርጌሃለሁ፤ አንተ እጅግ ተንቀሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ በአሕዛብ ዘንድ ታናሽ አድርጌሃለሁ፥ አንተ እጅግ ተንቀሃል። |
ይህንማ ያቀደው የሠራዊት አምላክ ነው፤ እርሱም ይህን ያቀደው ባደረጉት ነገር መታበያቸውን እንዲተዉ ለማድረግና የተከበሩትንም ሰዎች ለማዋረድ ብሎ ነው።
እንዲያውም ከሁሉ የደከመ መንግሥት ስለሚሆን ዳግመኛ ሌሎች መንግሥታትን የመግዛት ዕድል አይኖረውም፤ ከሁሉ ያነሰ ስለማደርገው ሌላ መንግሥት ማስገበር አይችልም።
ጠላቴም ይህን ሁሉ ያያል፤ “አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?” ይለኝ የነበረው ጠላቴ ኀፍረትን ይከናነባል፤ እኔ የጠላቴን ውድቀት አያለሁ፤ በመንገድ ዳር እንዳለ ጭቃ ሲረገጥም እመለከታለሁ።