ዘኍል 8:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤልን ሕዝብ ወክለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ እንዲያገለግሉና እስራኤላውያን ወደ ተቀደሰው ስፍራ በመቅረብ እንዳይቀሠፉ ይጠብቁአቸው ዘንድ፥ ሌዋውያንን ከእስራኤላውያን እንደ ስጦታ ተቀብዬ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያንን ወክለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚፈጸመውን አገልግሎት እንዲያከናውኑና እስራኤላውያን ወደ ተቀደሰው ስፍራ ቢቀርቡ እንዳይቀሠፉ ያስተሰርዩላቸው ዘንድ፣ ከእስራኤላውያን ሁሉ መካከል ሌዋውያኑን ስጦታ አድርጌ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻቸዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች ወደ መቅደሱ በቀረቡ ጊዜ መቅሠፍት እንዳያገኛቸው፥ ለእስራኤል ልጆች እንዲያስተስርዩላቸው፥ የእስራኤልንም ልጆች አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ እንዲሠሩ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለአሮንና ለልጆቹ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአቸዋለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌዋውያንንም ስጦታ አድርጌ አገባኋቸው፤ ልዩ በሆነች ድንኳን ውስጥ የእስራኤልን ልጆች ሥራ ይሠሩ ዘንድ፥ የእስራኤልንም ልጆች ኀጢአት ያቃልሉ ዘንድ ከእስራኤል ልጆች መካከል ለአሮንና ለልጆቹ ተሰጡ፤ ከእስራኤልም ልጆች ወደ መቅደስ የሚቀርብ አይኑር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ወደ መቅደሱ በቀረቡ ጊዜ መቅሠፍት እንዳያገኛቸው፥ ለእስራኤል ልጆች ያስተሰርዩላቸው ዘንድ፥ የእስራኤልንም ልጆች አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለአሮንና ለልጆቹ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአቸዋለሁ። |
በዚህ ፈንታ ሌዋውያንን በመገናኛው ድንኳንና በውስጡም ባሉት የመገልገያ ዕቃዎች ላይ ኀላፊዎች አድርገህ መድባቸው፤ እነርሱ ድንኳኑንና በውስጡ ያሉትን የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ይሸከማሉ፤ በድንኳኑም ውስጥ ያገለግላሉ፤ በዙሪያውም ይሰፍራሉ።
ነገር ግን ማንም ሰው ወደ ድንኳኑ በመቅረብ ቊጣዬን አነሣሥቶ የእስራኤልን ማኅበር እንዳያስፈጅ ሌዋውያን በድንኳኑ ዙሪያ ሰፍረው ይጠብቁት።”
ሙሴም አሮንን እንዲህ አለው፦ “የአንተን ጥና ወስደህ ከመሠዊያው የእሳት ፍም ጨምርበት፤ በፍሙም ላይ ዕጣን አድርግበት፤ ከዚያም ወደ ሕዝቡ በፍጥነት በመሄድ አስተስርይላቸው፤ ፍጠን! እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቊጣ ከመገለጡ የተነሣ በሕዝቡ መካከል መቅሠፍት ጀምሮአል።”
የታቦቱን ውስጣዊ ክፍል በመመልከታቸው እግዚአብሔር ተቈጥቶ ከቤት ሼሜሽ ሰዎች መካከል ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ እግዚአብሔርም ይህን ሁሉ እልቂት በመካከላቸው በማድረጉ የቤት ሼሜስ ሰዎች በማዘን አለቀሱ።