“ከእስራኤል ሕዝብም ሆነ ከእንስሶቹ በኲር ሆኖ የተወለደ ሁሉ ለእኔ መሆን ይገባዋል፤ ስለዚህ በኲር ሆኖ የተወለደውን ሁሉ ለእኔ እንዲሆን ቀድሰው።”
ዘኍል 8:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እነርሱን በኲር ሆነው ለሚወለዱት ለእስራኤላውያን ወንዶች ልጆች ሁሉ ምትክ አድርጌ ስለ መረጥኳቸው የእኔ ብቻ ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ሙሉ በሙሉ የእኔ እንዲሆኑ የተሰጡኝ እስራኤላውያን ናቸው፤ ከማንኛዪቱም እስራኤላዊት በተወለደ በኵር ወንድ ልጅ ምትክ የራሴ እንዲሆኑ ወስጃቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ከእስራኤል ልጆች መካከል ፈጽሞ ለእኔ ተሰጥተዋልና፤ በእስራኤል ልጆች በኵራት ሁሉ፥ ማኅፀን በሚከፍተው ሁሉ ፋንታ ለእኔ ወስጄአቸዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ከእስራኤል ልጆች መካከል ፈጽሞ ለእኔ ተሰጥተዋልና በእስራኤል ልጆች በኵራት ሁሉ፥ መጀመሪያ በሚወለድ ሁሉ ፋንታ ለእኔ ወስጄአቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ከእስራኤል ልጆች መካከል ፈጽሞ ለእኔ ተሰጥተዋልና፤ በእስራኤል ልጆች በኵራት ሁሉ፥ ማኅፀን በሚከፍት ሁሉ ፋንታ ለእኔ ወስጄአቸዋለሁ። |
“ከእስራኤል ሕዝብም ሆነ ከእንስሶቹ በኲር ሆኖ የተወለደ ሁሉ ለእኔ መሆን ይገባዋል፤ ስለዚህ በኲር ሆኖ የተወለደውን ሁሉ ለእኔ እንዲሆን ቀድሰው።”
“እነሆ ሌዋውያን የእኔ አገልጋዮች ናቸው፤ የግብጻውያንን በኲር ሁሉ በገደልኩ ጊዜ ከያንዳንዱ እስራኤላዊ የሚወለደውን በኲርና ከእንስሶቹም በኲር የሆነውን ሁሉ ለእኔ የተለየ እንዲሆን አድርጌ ነበር፤ አሁን ግን በኲር ሆነው የሚወለዱትን ወንዶች ልጆች የራሴ በማድረግ ፈንታ ሌዋውያንን መርጬአለሁ፤ እነርሱ የእኔ አገልጋዮች ይሆናሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
“እንግዲህ በኲር ሆነው በሚወለዱት እስራኤላውያን ወንዶች ልጆች ምትክ ሌዋውያንን ለእኔ ለይልኝ፤ እንዲሁም በኲር ሆነው በሚወለዱት የእስራኤላውያን እንስሶች ምትክ የሌዋውያንን እንስሳት ለእኔ የተለዩ እንዲሆኑ አድርግ።