“ከወላጆቹ አንዱ፥ ከልጆቹ አንዱ፥ ወይም ወንድሙ ወይም ያላገባች እኅቱ ካልሆኑ በቀር ማንኛውም ካህን የሌላ ሰው ሬሳ በመንካት ራሱን ማርከስ አይገባውም፤
ዘኍል 6:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአምላኩ ያቀረበው የናዝራዊነት ስእለት በራሱ ላይ ስለ ሆነ አባቱ ወይም እናቱ፥ ወንድሙ ወይም እኅቱ ቢሞቱ አስከሬናቸውን በመንካት ራሱን አያርክስ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራሱን ለእግዚአብሔር የለየበት ምልክት በራሱ ላይ ስላለ አባቱም ይሁን እናቱ፣ ወንድሙም ይሁን እኅቱ ቢሞቱ ለእነርሱ ሲል እንኳ ራሱን አያርክስ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአምላኩ ያደረገው ቅድስና በራሱ ላይ ነውና አባቱ ወይም እናቱ ወይም ወንድሙ ወይም እኅቱ ሲሞቱ ራሱን ስለ እነርሱ አያርክስ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአምላኩ ያደረገው ብፅዐት በራሱ ላይ ነውና አባቱ፥ ወይም እናቱ፥ ወይም ወንድሙ፥ ወይም እኅቱ ሲሞቱ ሰውነቱን አያርክስባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአምላኩ ያደረገው ስእለት በራሱ ላይ ነውና አባቱ ወይም እናቱ ወይም ወንድሙ ወይም እኅቱ ሲሞቱ ሰውነቱን አያርክስባቸው። |
“ከወላጆቹ አንዱ፥ ከልጆቹ አንዱ፥ ወይም ወንድሙ ወይም ያላገባች እኅቱ ካልሆኑ በቀር ማንኛውም ካህን የሌላ ሰው ሬሳ በመንካት ራሱን ማርከስ አይገባውም፤
ነገር ግን በድን ከመንካታቸው የተነሣ ያልነጹ ጥቂት ሰዎች ስለ ነበሩ በዚያን ቀን የፋሲካን በዓል ማክበር አልቻሉም፤ ስለዚህ እነርሱ ወደ ሙሴና አሮን ዘንድ ቀርበው እንዲህ አሉ፤